ጠ/ሚ ዐቢይ የሱዳን ሕዝቦች ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት የጀመሩትን የፖለቲካ ሂደት በስኬት ለመምራት ያላቸውን ጥበብ እና ብቃት አደነቁ

ጥር 18/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሱዳን ሕዝቦች ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት የጀመሩትን የፖለቲካ ሂደት በስኬት ለመምራት ያላቸውን ጥበብ እና ብቃት አድንቀዋል።

በተጀመረው የውይይት ሂደት ላይ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ያላትን አጋርነትም ገልጸዋል።

በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሱዳን ሪፐብሊክ ጉብኝታቸው ወቅት በተካሄደው ሁለተኛው ስብሰባ የሽግግር ሉዓላዊ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሌተና ጀነራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎን ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሱዳን ሕዝብ የራሳቸውን ችግር በራሳቸው ለመፍታት ያላቸውን ዕምቅ ዐቅም እንዲጠቀሙ አበረታተዋል።