ታኅሣሥ 11/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን የ2014 በጀት ዓመት እና የ2015 ሩብ ዓመት አፈጻጸም ገመገሙ::
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከወራት በፊት የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር አመራሮችን ሰብስበው እንደነበር ይታወሳል።
በስብሰባውም በ100 ቀናት ዕቅድ ተግባራዊ የሚደረጉ ጉዳዮችን በተመለከተ አቅጣጫ አስቀምጠው እንደነበር አይዘነጋም።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመስተዳድሩን አመራሮች ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው በድጋሚ አግኝተው የከተማዋን የ2014 በጀት ዓመት እና የ2015 ሩብ ዓመት አፈጻጸም ገምግመዋል።
በዚህም በከተማዋ የተጀመሩ መልካም የልማት ሥራዎች እንዲስፋፉ፣ ችግሮችም እንዲስተካከሉ አቅጣጫ መስጠታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።