ፋሲል ከነማ እና ባህርዳር ከተማ አቻ ተለያዩ

ሚያዝያ 05/2013 (ዋልታ) – በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሳምንት ፋሲል ከነማ እና ባህርዳር ከተማ 0ለ0 በሆነ ውጤት አቻ ተለያይተዋል።

ሊጉን ፋሲል ከነማ በ17 ጨዋታዎች በሰበሰበው 42 ነጥቦች ሲመራ ኢትዮጵያ ቡና በበተመሳሳይ ጨዋታዎች በ33 ነጥቦች ሁለተኛ፣ ባህርዳር ከተማ ደግሞ በ30 ነጥቦች 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።