ፋሲል ከነማ ከሂውማን ብሪጅ ኢትዮጵያ ጋር የትጥቅ አቅርቦት ስምምነት ተፈራረመ

ግንቦት 26 / 2013 (ዋልታ) – ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ከሂውማን ብሪጅ ኢትዮጵያ ጋር የትጥቅ አቅርቦት ስምምነት አደረገ።
በስምምነቱ መሰረት ሂውማን ብሪጅ ኢትዮጵያ ለፋሲል ከነማ ከ5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የመጫዎቻ ጫማ፣ ኳስ፣ ማሊያዎችና የማሰልጠኛ ቁሳቁሶች በድጋፍ መልክ እንደሚሰጥም ተገልጿል ፡፡ድርጅቱ ከዚህ ቀደም ለክለቡ አንድ ሚሊየን ብር የሚገመት የስፖርት ትጥቆችን ድጋፍ ማድረጉም ተጠቁሟል ፡፡
ስምምነቱ የድርጅቱ ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ለማ አታክልቲ እና የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ አብዮት ብርሃኑ በተገኙበት መከናወኑን ከክለቡ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።