ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል ማረጋገጥ የከተማ አስተዳደሩ ቀዳሚ ተግባር ነው- ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ሚያዝያ 21/2013 (ዋልታ) – ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል ማረጋገጥ የከተማ አስተዳደሩ ቀዳሚ ተግባር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ምክትል ከንቲባዋ ይህንን ያሉት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች የቀበሌ ቤት ባስረከቡበት ወቅት ነው፡፡

በክፍለ ከተማው ለነዋሪዎቹ የተላለፉት 115 የሚሆኑ የቀበሌ ቤቶች መሆናቸውም ተገልጿል፡፡

በህገወጥ መንገድ የተያዙ የቀበሌ ቤቶችን በማስለቀቅ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎቹ መሰጠቱንም ወ/ሮ አዳነች ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም 65 ለሚሆኑ አንቀሳቃሽ ማህበራት 1050 ካሬ የመሥሪያ ቦታ አስረክበዋል፡፡

(በሰለሞን በየነ)