ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ከአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ጋር ተወያዩ

ነሀሴ 17/2013 (ዋታል) –ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ባለፈው ወር የተሾሙትን የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አኔት ዌበርን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ውይይቱ በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ህብረት ስላለው ግንኙነት እና በልዩ መልዕክተኛዋ ተልእኮዎች ላይ ያተኮረ መሆኑንም ከፅህፈት ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።