ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ አምባሳደሮችን አሰናበቱ

ጥቅምት 3/2014 (ዋልታ) – ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ በኢትዮጵያና አፍሪካ ኅብረት የአረብ ሊግ አምባሳደር እና በኢትዮጵያ የኮትዲቯር አምባሳደርን አሰናብተዋል፡፡

በኢትዮጵያና አፍሪካ ኅብረት የአረብ ሊግ አምባሳደር ሳሌህ ሳህቡን እና በኢትዮጵያ የኮትዲቯር አምባሳደር ያፕል ኮፊን ማሰናበታቸውን ከፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡