ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ የብሄራዊ የጀግኖችና የህጻናት አምባ የበላይ ጠባቂ ሆኑ

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የብሄራዊ የጀግኖችና የህጻናት አምባ የበላይ ጠባቂ እንዲሆኑ በብሄራዊ የጀግኖችና የህጻናት አምባ የቦርድ አባላት የቀረበላቸውን ጥያቄ ተቀብለዋል።

ፕሬዚዳንቷ የብሄራዊ የጀግኖችና የህጻናት አምባ የቦርድ አባላት ጋር ተወያይተዋል።

የቦርዱ አባላት ማህበሩ የተጎዱ ጀግኖችንና ቤተሰቦቻቸውን ለመርዳትና ለመንከባከብ የተቋቋመ መሆኑን በመግለጽ፤ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ የማህበሩ የበላይ ጠባቂ እንዲሆኑም ጠይቀዋል፡፡

ፕሬዝዳንቷም የማህበሩ ዓላማ የተቀደሰና በጣም አስፈላጊ፣ መበረታታት ያለበት መሆኑን “ጀግኖችን መንከባከብ የማህበረሰብ ግዴታ ነዉ” በማለት የበላይ ጠባቂነት ጥያቄውን መቀባላቸውን ከፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።