በሰላም ማስከበር ወቅት የተጎዱ መሰረተ ልማቶችን በመጠገን የመማር ማስተማሩ ስራ በሁሉም ቦታ ይጀምራል- የትምህርት ሚኒስቴር

በትግራይ በትግራይ ክልል የተጎዱ መሰረተ ልማቶችን በመጠገን ትምህርት ለማስጀመር 50 ሚሊየን ብር በጀት መያዙን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሚሊየን ማቲዎስ ገለጹ።

በአማራ ክልል አጎራባች አካባቢዎች በህግ ማስከበር ሂደቱ የተጎዱ ትምህርት ቤቶችን በመጠገን ወደ ስራ ለማስገባትም እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።

ለትግራይ ክልልም ከ700 ሺህ በላይ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል መዘጋጀቱንም ጠቁመዋል።

ሚኒስቴሩ ትምህርት በሁሉም አካባቢ እንዲጀመር ለማድረግ እየሰራ መሆኑ ይታወሳል። መረጃውን ያገኘነው ከትምህርት ሚኒስቴር ነው፡፡