ታኅሣሥ 12/2014 (ዋልታ) የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ከኮሮና ቫይረስ አገግመው ወደ ሥራ መመለሳቸውን ጽህፈት ቤታቸው አስታወቀ።
የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸው ለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩት ፕሬዝዳንቱ አሁን ወደ መደበኛ ሥራቸው መመለሳቸው ተገልጿል፡፡
ፕሬዝዳንት ራማፎሳ ባለፈው ዓመት የካቲት ላይ ጆንሰን እና ጆንሰን የተሰኘውን ክትባት ወስደው እንደነበርም ተመላክቷል፡፡
ፕሬዝዳንቱ ከኮሮና አገግመው መደበኛ ሥራቸው ላይ እንደሆኑ የተገለጸ ሲሆን የአውሮፓውያኑ 2021 የመጨረሻ የካቢኔ ስብሰባም ከነገ በስቲያ እንደሚመሩ ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ ከሰሞኑ ባደረጉት ምርመራም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጠ በኋላ ቀለል ያሉ ምልክቶች ታተውባቸው ህክምና ሲከታተሉ እንደነበር መገለጹ ይታወሳል፡፡
ራማፎዛ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተከትሎ መንግስታዊ ኃላፊነታቸውን ለአንድ ሳምንት ለምክትላቸው ዴቪድ ማቡዛ በውክልና መስጠታቸው ይታወቃል።
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
https://www.facebook.com/waltainfo
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
https://bit.ly/3vmjIZR
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/WALTATVEth
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!