ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የሕዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌት በስኬት በመጠናቀቁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ሐምሌ 12/2013 (ዋልታ) – የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌት በስኬት በመጠናቀቁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ፕሬዳዳንቷ በደስታ መግለጫቸው፣ “ለመላው ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም ሌት ተቀን በግድቡ ሥራ ላይ ለሚሳተፉ ሁሉ በራሴ እና በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ስም እንኳን ደስ ያላችሁ! በርቱ!!” ብለዋል።
“የኢትዮጵያ ሀገራችን ብርቱ ልጆች ያለባቸው ከፍተኛ ውስጣዊ እና ውጫዊ ጫና ሳይበግራቸው ግድባችንን እዚህ ደረጃ ማድረሳቸው እጅግ ያስመሰግናቸዋል” ሲሉም አክለዋል።