ፕሮፌሠር ካሣሁን ብርሀኑ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የካቲት 15/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም ዐቀፍ ግንኙነት (PSIR) ትምህርት ክፍል መምህር እና ተመራማሪ የነበሩት ካሣሁን ብርሀኑ (ፕ/ር) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

ካሣሁን ብርሀኑ (ፕ/ር) በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ የካቲት 15/2014 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የአዲስ አበባ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት አሳውቋል።

ላለፉት 36 ዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነትና ተመራማሪነት እንዲሁም በልዩ ልዩ ከፍተኛ የኃላፊነት ዕርከኖች ማገልገላቸውም ተጠቁሟል።

በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ የተለያዩ ማኅበራዊ አገልግሎቶችን በማበርከትም ይታወቁ ነበር፡፡

የቀብር ስነ ሥርዓታቸው ነገ የካቲት 16 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 በየካ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት እንደሚፈጸም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡