1 ሺሕ 22 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

ግንቦት 10/2014 (ዋልታ) በዛሬው ዕለት በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳዑዲ ዓረቢያ የመመለስ ሥራ 1 ሺሕ 22 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡
ከተመላሾች ውስጥም 108 ሴቶች ሲሆኑ ዘጠኝ ሚሆኑት ደግሞ ህጻናት መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ ተደርጓል፡፡
እስካሁን ድርስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ሥራ ቁጥራቸው ከ24 ሺሕ 660 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን ከሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡