11ኛው የበጎ ሰው ሽልማት ጳጉሜን 5 እንደሚካሄድ ተገለጸ


ነሐሴ 17/2015 (አዲስ ዋልታ) 11ኛው የበጎ ሰው ሽልማት መርኃ ግብር ጳጉሜን 5/2015 እንደሚካሄድ የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት ቦርድ አስታወቀ።

ቦርዱ የዘንድሮውን የበጎ ሰው ሽልማት አስመልክቶ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ሽልማቱ በጎ ሰዎችን በመሸለም ሌሎች በጎ ሰዎች እንዲበራከቱ በመስራት ላይ ይገኛል ብሏል።

ድርጅቱ ከየካቲት 1 እስከ ሚያዝያ መጨረሻ ድረስ የበጎ ሰው ተሸላሚዎችን ጥቆማ መቀበሉን ገልጿል።

የበጎ ሰው ሽልማት እውቅና ከሚሰጣቸው ዘርፎች መካከል መምህርነት፣ መንግስታዊ ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በጎ አድራጎት፣ ኪነጥበብ፣ ሚዲያ እና ኮሙዩኒኬሽን እንዲሁም ሌሎች ዘርፎች ተካተውበታል።

በዕለቱም በዘጠኝ ዘርፎች ለተመረጡ ኢትዮጵያዊያን እውቅና እንደሚሰጣቸው መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።