በዓለም ላይ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ ህዝቦች ለኮሌራ በሽታ ተጋላጭ መሆናቸው ተገለጸ

ታኅሣሥ 17/2015 (ዋልታ) በዓለም ላይ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ ህዝቦች ለኮሌራ በሽታ ተጋላጭ መሆናቸው ተገለጸ፡፡

ወረርሽኙ እየተስፋፋባቸው ከሚገኙ አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንደኛዋ መሆኗ የተገለጸ ሲሆን የወረርሽኙን የስርጭት አቅም ለመቀነስ እና ለመቆጣጠር በሀገር አቀፍ ደረጃ የተለያዩ ፕሮግራሞች ተቀርፀው ሲሰሩ መቆየታቸው ተገልጿል::

በዋናነት በሽታውን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የክትባት ዘመቻዎችን ማዳረስ፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን ማሻሻል እንዲሁም የአመራር ሥርዓትና ትብብርን ማሳደግ እንደሚገባ የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገልጸዋል::

በዚህም ኮሌራን በቀጣዮቹ ስድስት ዓመታት ውስጥ ለመቆጣጠር መታቀዱ ተገልጿል::

ኮሌራን ለመቆጣጠር እና በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2030 ከዓለም ለማስወገድ የታያዘውን ግብ እንደ ሀገር ለማሳካት በቅንጅት በመስራት የማህበረሰብን የግንዛቤ አድማስ ማስፋት ያስፈልጋል ተብሏል::

በዚህም ኢትዮጵያ ኮሌራን ለመቆጣጠር በዓለም የጤና ድርጅት ከተያዘው እቅድ ከሁለት ዓመት ቀድማ መቆጣጠር እንድትችል ይሰራልም ነው የተባለው::

በሔብሮን ዋልታው