14ኛው የስልጤ ባህል፣ ታሪክና ቋንቋ ሲምፖዚየም እየተከበረ ነው

መጋቢት 26/2013 (ዋልታ) – 14ኛው የስልጤ ባህል፣ ታሪክና ቋንቋ ሲምፖዚየም  በወዳጅነት አደባባይ እየተከበረ ነው፡፡

እንዲሁም የስልጤ ዞን እራሱን በራሱ ማስተዳደር የጀመረበት 20ኛ ዓመት እየተከበረ ይገኛል፡፡

በመርሃ ግብሩ  የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ የዞኑ የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ሲምፖዚየሙ በዞን ደረጃ በወራቤ ከተማ መከበሩ ይታወሳል፡፡