የኢትዮ-አሜሪካን ግንኙነት የሚያጠናክር የህዝብ ጉዳዮች ተቋም ተመሰረተ

መጋቢት 26/2013 (ዋልታ) – የኢትዮ-አሜሪካን ግንኙነት የሚያጠናክር  የህዝብ ጉዳዮች (AEPAC)ተቋም ተመስርቷል።

አምባሳደር ፍጹም አረጋ የኢትዮጵያ ዳያስፖራን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ  ጠቁመው ተቋሙ የሁለቱ ሀገራትን  ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚያግዝ እምነታችን ነው ብለዋል።

አምባሳደሩ ተቋሙን ያቋቋሙትን ባለ ራዕይዎች እና ይህን ራዕይ የተጋሩ የሲቪክ ማህበራት መሪዎችን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አመስግነዋል።

አምባሳደር ፍጹም አረጋ አያይዘውም የኢትዮጵያ ኤምባሲም ለመተባበር ዝግጁ ነው ብለዋል፡፡