16ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በአዲስ ዋልታ ግቢ ተከበረ

የአዲስ ዋልታ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መሐመድ ሀሰን

ጥቅምት 5/2016 (አዲስ ዋልታ) 16ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ዛሬ በአዲስ ዋልታ ቅጥር ግቢ ውስጥ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት ተከብሯል፡፡

በዚሁ ወቅት የአዲስ ዋልታ ዋና ስራ አስፈጻሚ መሐመድ ሀሰን እንደገለጹት ባንዲራ የሀገራችንም ሆነ የራሳችን ማሳያ ምልክት እንጂ የንትርክ መንስኤ ሊሆን አይገባም ብለዋል።

ሀሳብ ይሞታል፣ አመለካከትም ይቀየራል፤ ሊሞትና ሊቀየር የማይችለው ግን የሀገር ፍቅር ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው የሀገር ፍቅር ደግሞ የሚገለፀው በሰንደቅ አላማ ነው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ይህ ባንዲራ ብዙዎች ህይወታቸውን የሰጡለት የነፃነታችን ተምሳሌት በመሆኑ ሁልጊዜም በልባችን ልናኖረው ይገባል ብለዋል አቶ መሐመድ ሀሰን።

የአዲስ ዋልታ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ እመርታ አስፋው በበኩላቸው ሰንደቅ ዓላማ እያንዳንዱ ነገራችንን የምንገልፅበት ልዩ ምልክታችንና መግባቢያ ቋንቋችን ነው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ እመርታ አስፋው

የአዲስ ዋልታ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ዳውድ መሐመድ በበኩላቸው የሰንደቅ ዓላማ ቀን የአንድነታችን መገለጫ በመሆኑ በአንድንት ልንቆምለት ይገባል ብለዋል፡፡

ዳውድ መሐመድ

በዕለቱ የፌዴራል ፖሊስ ባልደረቦች፣ የአዲስ ዋልታ ሰራተኞችና አመራሮች በተገኙበት በኢትዮጵያ ህዝብ ብሔራዊ መዝሙር ታጅበው ሰንደቅ ዓላማ በክብር የመስቀል ስነ ስርዓት ተካሂዷል፡፡

በቴዎድሮስ ሳህለ