በትግራይ የታቀደው 28ሚሊየን ኩንታል ሰብል ምርት ሊሳካ ይችላል

ዘንድሮ የተከናወኑ ምርታማነትን የማሳደግ የሚያስችሉ ስራዎች የታቀደው 28 ሚሊየን ኩንታል ሰብል ምርት ሊታፈስ እንደሚችል ተስፋ መደረጉን የትግራይ ክልል እርሻና ገጠር ልማት ቢሮ አስታወቀ ፡፡

በክልሉ የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ልዩ ልዩ ስራዎች በመከናወናቸው የተሻለ የዝናብ ስርጭ በመገኘቱ 1 ሚሊየን 209 ሺ 395  በላይ ሄክታር የተሸፈነው ሰብል በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የቢሮው የክረምት ሁኔታዎችና ቴክኖሎጂ ዕድገት የስራ ሂደት ባለቤት አቶ ንጉሰ ተኽሉ ገልጸዋል ፡፡

ኪዚሁም ውስጥ የተሻለ ምርት ለማፈስ እንዲቻል በክልሉ ከ46 ሚሊየን በላይ ኩንታል ፍግና ኮፖስት በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ መበተኑን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም 408 ሺ 176 ሄክታር በመስመር እና 443 ሺ 967 ሄክታር ደግሞ በማዳበሪያ እንዲዘራ መደረጉን አብራርተዋል ፡፡

አርሶ አደሩ ምርቱን ለማሳደግ 77 ሺ 880 ኩንታል ምርጥ ዘር መጠቀሙን ጠቁመዋል፡፡