የድምፅ ሞገድ ንዝረትን ወደ ኤሌክትሪክ በመቀየር ስማርት ስልኮችን ሀይል የሚሞላ አዲስ ፈጠራ

በስማርት ስልክ ተጠቃሚዎች ዘንድ የስልኬ ባትሪ ቶሎ ቶሎ እየዘጋ አስቸገረኝ የሚሉ ነገሮችን መስማት የተለመደ ነው።

“ኒኮላ ላብስ” የተባለ ኩባንያ ግን ለዚህ መፍትሄ የሚሆን አዲስ ፈጠራ አግኝቻለው፤ በቅርቡም እጃቹ ይገባል ሲል አስታውቋል።

ኩባንያው በስልካችን በምንነጋገርበት ጊዜ የሚፈጠር የድምጽ ሞገድ ንዝረትን ወደ ኤሌክትሮ ማግኔቲክ በመቀየር ስልካችን በቀላሉ ሀይል እንዲሞላ የሚያስችል ፈጠራ ነው በመስራት ላይ የሚገኘው።

የድምጽ ሞገድ ንዝረትን ወደ ሀይልነት እንዴት ይቀይራል? ለሚለው የድምጽ ሞገድን ወደ ኤሌክትሪክ ሀይልነት በሚቀይር የስልክ ሽፋን /ከቨር/ አማካኝነት መሆኑን ኩባንያው አስታውቋል።

የስልክ ሽፋኑን በስልካችን ላይ አልብሰን በስልኩ በምናወራበት ጊዜ ሽፋኑ የድምጽ ሞደግ ንዝረቱን ወደ ሀይልነት በመቀየር የስልካችን ባትሪ እንዲሞላ ያደርጋል።

በዚህም ስልካችን ቢያንስ እስከ 30 በመቶ ሀይል እንዲያገኝ በማድረግ የስልካችን ባትሪ ሀይል ቆይታን ሊያራዝም ይችላል ነው የተባለው።

ይህ ማለት ግን ስልካችንን በቀጥታ ከኤሌክትሪክ ቻርጅ ማድረግ የለብንም ማለት አይደለም ተብሏል።

አዲሱ ፈጠራ የባትሪ ቆይታን ለማርዘም እንጂ ሀይል ሙሉ በሙሉ ለመሙላት እንደማያችልም ተነግሯል።(ኤፍ.ቢ.ሲ)