ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ሆነው ተሾሙ

የቀድሞው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት የኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሞትን ተከትሎ የግድቡን ግንባታ ኢንጂነር ኤፍሬም ወ/ኪዳን ላለፉት ሁለት ወራት በጊዚያዊነት ሲመሩት ቆይተዋል፡፡

በመሆኑም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ለግድቡ ግንባታ ስራ አስኪያጅ እና ሁለት ምክትል ሥራ አስኪያጆች ኃላፊነት ሰጥተዋል፡፡

በዚሁ መሰረት ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ከዛሬ ጀምሮ የታቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ስራ አስኪያጅ ሆነው ሲሾሙ፣ኢንጂነር ኤፍሬም ወልደኪዳን እና አቶ ፍቃዱ ከበደ ደግሞ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሆነው እንዲሰሩ መመደባቸውን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የውጭ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ለዋልታ የላከው መግለጫ ያስረዳል፡፡