ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት ሊ ዮንግ ጋር ተገናኝተው ተወያዩ።

ውይይታቸው በዋናነት በኢትዮጵያ ውስጥ የተቀናጀ የግብርና ኢንዲስትሪ ፓርኮችን ለማጠናከር የድርጅቱ ድጋፍ ቀጣይነት ላይ ያተኮረ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ገልጸዋል።

የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርኮች የግብርና ምርታማነትን በማረጋገጥ፣ እሴትን በመጨመርና የኢትዮጵያዊያንን ኑሮ በማሻሻል የአገሪቱን ኢኮኖሚ መዋቅር ያሸጋግራሉ ተብሎ ይጠበቃል ። (ምንጭ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት)