የህዳሴ ግድብ ግንባታ ከአራት ዓመት በኋላ እንደሚጠናቀቅ ተገለጸ

በኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ያሉትን  የተለያዩ  ክፍተቶችን በማስተካከል ገድቡን  ከአራት ዓመት በኋላውይም  እኤአ በ2022   እንደሚጠናቀቅ ተገለፀ።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ የግንባታ ሁኔታን በተመለከተና የግንባታ ደረጃ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው።     

የህዳሴ  ግድብ ጥልቅ ጥናትና ምርምር ስራ ሳይከናወንለት ግንባታው በመጀመሩ ምክንያት የግንባታ ጊዜው ሊጓተት እንደቻለ የውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴርም  ገልጿል።

የታላቁ የኢትዮዽያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ያስከተለው ጉዳት ሀገሪቷ በየዓመቱ 800 ሚሊየን ዶላር እንድታጣም ሆኗል ተብሏል ።

በዚህም በሳሊኒ ሲሰራ የነበረው የሲቪል ምህንድስናው ስራው 82 በመቶ ላይ የሚገኝ ሲሆን፥ የኤሌክትሮ መካኒካል ሥራው ደግሞ 25 በመቶ ደረጃ  ላይ ይገኛል የሚገኝ መሆኑን  በውይይቱ ተጠቅሷል ።

በአጠቃላይ የህዳሴ ግድብ ግንባታ 65 በመቶ ላይ መድረሱ በተካሄደው ውይይት ላይ ተገልጿል  ። 

የግንባታው ጽህፈት ቤት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና ከውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ  ሚኒስቴር የግንባታ ሂደቱን ለማፋጠን በትብብር እየሰሩ ይገኛሉ።

የህዝባዊ ተሳትፎን ፣ ከታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ጋር ባለው የሶስትዮሽ ግንኙነት እና የኃይል ሽያጭ ትስስር ላይ ትኩረት ባደረጉ አራት ጉዳዮች ላይ ነው ውይይቱ እየተካሄደ የሚገኘው።