የትግራይ ክልል መንግስት በእሬቻ በዓል ለሞቱት ሐዘኑን ገለጸ

በቢሾፍቱ ከተማ ትናንት በደማቅ ስነ ስርዓት ተጀምሮ የነበረው ዓመታዊ የኦሮሞ እሬቻ በዓል ጽንፈኛ ነውጠኞች በፈጠሩት ሁከት ለደረሰው አስከፊ የህይወት መጥፋት አደጋ የትግራይ ክልል መንግስት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘኑን ገለጸ

በዚሁ የኦሮሞ ባህላዊ እሴት መግለጫ የሆነው የእሬቻ በዓል አጋጣሚውን ሲፈልጉ የነበሩት ኦነግና ተላላኪዎቹ በቁጥጥር ስር ለማዋልና ወደ ህግ ለማቅረብ በፌደራል መንግስት ለሚደረገው  ጥረት የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ አስታውቌል ።

የህግ የበላይነትና ሰላም በጸረ ሰላም ሃይሎች በሚፈጥሩት ሁከት እንደማይደናቀፍ ደግሞ መንግስት አስገንዝበል ።