የሶርያ መንግስት የተቃዋሚ ተዋጊዎች ከአሌፖ ከተማ ለቀው እንዲወጡ አሳሰቡ።

የመንግስት ጦር ለተቃዋሚዎች ሰላማዊ የመውጫ መንገድ እንደሚከፍቱላቸውና የአርዳታ አቀርቦት እንደሚያደረግላቸው መግለፁም ነው የተሰማው።

ነገር ግን የተቀዋሚ ሃይሎች ለጥያቄው ስለሰጠው ምላሽ በዘገባው የተባለ ነገር የለም።

በከፍተኛ ጦርነት ውስጥ የምትገኘው የሶርያዋ ሁለተኛ ትልቋ ከተማ አሌፖ በአሜሪካ እና ሩስያ መካከል ተደርሶ የነበረው የተኩስ አቁም ስምምነት ባለፈው ወር መጨረሻ ላይ መፍረሱን ተከትሎ ጦርነቱ ይበልጥ አገርሽቶባታል ቢቢሲን ጠቅሶ ኤፍ.ቢ.ሲ ዘግቧል ።