ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር የሙከራ ምርት የጀመረውን የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ጎበኙ።
በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት ፕሬዚዳንት አልበሽር ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር በመሆን ነው ፋብሪካውን ትናንት የጎበኙት።
ግንባታው ሁለት ዓመት የፈጀው የኦሞ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ በቅርቡ በሙከራ ደረጃ ማምረት መጀመሩ ይታወቃል።
ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ስኳር 2 ነጥብ 8 ሚሊየን ሊትር ኢታኖል በዓመት ያመርታል ተብሎ ይጠበቃል።
በቻይና ኩባንያ የተገነባው ፋብሪካው የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ስር እየተገነቡ ካሉት አራት ፋብሪካዎች ውስጥ ወደ ስራ በመግባት ቀዳሚ መሆኑን ኢቢሲ ዘግቧል።