ህገ መንግስቱ ሳይሸራረፍ ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ የሁሉም ዜጎች ኃላፊነት ነው-ፕሬዚዳንት ሙላቱ

የኢፌዴሪ ህገ መንግስት ሳይሸራረፍ ተግባራዊ የሚሆንባቸውን መንገዶች ሁሉ መጠበቅ የሁሉም ዜጎች ኃላፊነት መሆኑን ፕሬዚደንት ሙላቱ ተሾመ ገለፁ።

ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሉት 12ኛውን የኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦች ቀንን አስመልክተው ዛሬ በብሔራዊ ቤተመንግስት ለመላው ህዝብ ባስተተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ነው።

ኢትዮጵያ የብዙ ብሔር ብሔረሰቦች፣ ባህሎች፣ ቋንቋዎችና ሃይማኖቶች ባለቤት መሆኗን በመልዕክታቸው ጠቅሰዋል።

ሆኖም ቀደም ባሉት ስርዓቶች እነዚህን የሚያስተሳስር ስራ ባለመሰራቱ አንድነቱ የላላ እንደነበር ነው ፕሬዚዳንት ሙላቱ የገለፁት።

ህዳር 29 ቀን 1987 . የፀደቀው ህገ መንግስት ያረጋገጠው ዴሞክራሲያዊ ስርዓትና ይህ ቀንም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ተብሎ እንዲከበር ከተወሰነበት 1998 . ወዲህ የአንድነት ትስስሩ እየተጠናከረ መጥቷልብለዋል።

የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን የሀገሪቱን ህዝቦች የበለጠ ከማስተዋወቅ ባሻገር አንድ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ማህበረሰብ በመፍጠር ረገድ ትልቅ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።

በዓሉ ላለፉት 11 ዓመታት በተከታታይ የህዝቡን ተሳትፎ ባረጋገጠ ሁኔታ በድምቀት ሲከበር ቆይቷል።

ሂደቱም የሀገሪቱ ህዝቦች የበለጠ እንዲተዋወቁ እና አንድ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ማህበረሰብ በመፍጠር ረገድ ትልቅ ድርሻ አለው ብለዋል፡፡

የህገ መንግስቱ መፅደቅ የህዝቦች መጪ ጊዜ የሰላም የመረጋጋት የብልጽግና እንዲሆን ያላቸውን ጽኑ ፍላጎት በግልጽ ያሳዩበት ታላቅ ታሪካዊ ክስተት ነው ብለውታል፡፡

በዓሉን ስናከብር ሀገሪቱን ከድህነት እና ኋላቀርነት ለማላቀቅ የገባነውን ቃል የምናድሰበት ሊሆን ይገባል ነው ያሉት።

ሀገሪቱ ከድህነትና ኋላ ቀርነት በመላቀቅ ወደ ብልፅግና ጎዳና በመጓዝ ላይ በመሆኗ፥ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎችና ባለሀብቶች ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ እያደረጓት መሆኑን ነው ያነሱት።

ህገ መንግስቱ መሰረታዊ የሆኑ ሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲካተቱበት መደረጉ ለሀገር ግንባታ ሂደቱ ከፍተኛ ሚና መጫወቱን  ገልፀዋል።

ዜጎች በህገ መንግስቱ ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ለማስፋት ከበዓላት ወቅት ባለፈ ወጥ በሆነ መልኩ ሊሰራበት ይገባልም ነው ያሉት።

ስለሆነም የህገ መንግስቱ ትሩፋቶችን ለማስቀጠል ሁሉም ዜጋ ለተግባራዊነቱ እንዲረባረብ አጥሪ አቅርበዋል።

ፕሬዚዳንት ሙላቱ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ 12ተኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በአል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል(ኤፍ )