መንግስት ለ746 ታራሚዎችና ተጠርጣሪዎች ይቅርታ እንደሚያደርግላቸውና ክስ እንደሚያቋርጥላቸው አስታወቀ

መንግስት ለ417 ፍርደኞች ይቅርታ እንደሚያደርግ እና ለ329 ተጠርጣሪዎች ክስ እንደሚያቋርጥ የፌደራል ጠቅላይ ዋና ዓቃቢ ሕግ አቶ ጌታቸው አምባዬ አስታወቁ ፡፡

አቶ ጌታቸው በተለይ ለዋልታ እንደገለጹት ፤ከታራሚዎቹ ውስጥ 298 በፌደራል ማረሚያ ቤት እና 119 በአማራ ክልል ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ መሆናቸውን ነው ያብራሩት ።

እንደዚሁም ክሳቸው እንዲቋረጥ የተወሰነላቸው ተጠርጣሪዎች 278 በፌደራል፣ 33 በትግራይ ክልልና 18 በአማራ ክልል የሚገኙ መሆናቸውን ጠቁመዋል ።

እንደ አቶ ጌታቸው ገለጻ፤ ይቅርታውና የክስ ማቋረጡ የሚደረገው የእስረኞች ጉዳይ ለሀገሪቱ ርእሰ ብሄር ቀርቦ ከጸደቀና ተገቢ ስልጠና ካገኙ በኋላ ነው ፡፡

ቀደም ሲል በአዲስ አበባ አስተዳደር ፣በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች 6ሺህ 376 በፈጸሙት ጥፋት ታራሚዎችና ተጠርጣሪዎች ክስ ተቋርጦ መንግስት ባደረገላቸው ይቅርታና ምህረት ከእስር መለቀቃቸው ይታወቃል ።