የቻይና ብሔራዊ ህዝባዊ ኮንግረስ ሊቀመንበር ሊ ዛንሹ ከፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ጋር ተወያዩ

የቻይና ብሔራዊ ህዝባዊ ኮንግረስ ሊቀመንበር ዛንሹ ከኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ጋር በብሔራዊ ቤተመንግስት ተወያይተዋል፡፡

ሊቀመንበሩ በአፍሪካ ያደረጉት የመጀመሪያ ጉብኝታቸው ሲሆን፤ በኢትዮጵያ በቅርቡ የተደረገውን ሰላማዊ የስልጣን ሽግግርን እንደሚያደንቁ ገልፀዋል፡፡

በቻይና እና ኢትዮጵያ መካከል ያለውን የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰራና ቻይናም አጋሪነቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል አስረድተዋል፡፡

ውይይቱን የተከታተሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም ቻይና ቀዳሚ የኢትዮጵያ አጋር ሀገር መሆኗን የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ መግለፃቸውን ጠቅሰው ኢትዮጵያም ለቻይና ወዳጅነት ትልቅ ቦታ የምትስጥ መሆኗን አንስተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ተሞክሮ በምሆንበት ደረጃ በቀጣይ እንደምሰራም አረጋግጠዋል፡፡

የአፍሪካ ሀገራት በቻይና አፍሪካ ፎረም በሚያደርጉት ግንኙነት ኢትዮጵያ ዋነኛ ድልድይ እንደሆነችና በኢትዮጵያ የሚታየውን ልማት ወደ ሌሎች ሀገራት ለማስፋት የቻይና መንግስት እንደሚሰራም የቻይና ብሄራዊ ህዝባዊ ኮንግረስ ሊቀመንበር ዛንሹ  ገልጸዋል፡፡