የቀድሞ የደርግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት አዲስ አበባ ገቡ

የቀድሞ የደርግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት የሆኑት አምባሳደር ካሣ ከበደና ተክሌ የሻው አዲስ አበባ  ገቡ ።

የቀድሞ የደርግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በዛሬው ዕለት ቦሌ አለም አቀፍ  የአውሮፕላን  ማረፊያ  በኩል  ነው  ወደ አገር ውስጥ የገቡት ።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ በአገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቃዋሚ  ኃይሎች ወደ አገራቸው  ተመልሰው ገብተው ሰላማዊ  ትግል  እንዲያደርጉ  ጥሪ ማቅረባቸው  ይታወሳል ።