ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጠንካራ አቅም እንዲፈጥሩ በጠቅላይ ሚንስትሩ የቀረበላቸውን ጥሪ እንደሚቀበሉ ገለጹ

ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሰባሰበው ጠንካራ አቅምን በመፍጠር ብቁ እና ተፎካካሪ ለመሆን የሚያስችላቸው አቅም እንደፈጥሩ በኢፌድሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የቀረበላቸው ጥሪ እንደሚቀበሉ ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትሩ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ባደረጉት ውይይት በሀገሪቷ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቁጥር መብዛት ጠንካራ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ እንዳይኖር አድርጓል ማለታቸው ይታወሳል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተመሳሳይ ፍልስፍና እና ርዕዮት ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ አንድ በመምጣት ብቁ እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ መክረው ነበር፡፡

ተፎካካሪ ፓርቲዎች የጠቅላይ ሚንስሩ ጥሪ በህዝብም እየቀረበላቸው መሆኑን ገልጸው ሃሳቡን መቀበል ወቅቱ የሚፈልገው ተግባር መሆኑን ተናግረዋል፡፡