በጅግጅጋ ከተማ በተለያዩ ዘርፎች ተደራጅተው የተሰማሩ ወጣቶች ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣታቸውን ተናገሩ

በጅግጅጋ ከተማ በተለያዩ ዘርፎች ተደራጅተው የተሰማሩ ወጣቶች ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣታቸውን ተናገሩ፡፡

በከተማዋ 9 በመሆን በማህበር የተደራጁ ወጣቶች በፈሳሽ ሳሙና መምረት ስራ ተሰማርተው በአጭር ጊዜ ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣታቸውን ገልጸዋል፡፡

በስራ ዙሪያ ለሶስት ተከታታይ ወራት ስልጠና በመውሰድ ስራ የጀመሩት ወጣቶች በስራቸው ገቢ በማግኘት ውጤታማ ከመሆናቸው ባሻገር ለሌሎች ወጣቶች ስራ ዕድል እየፈጠሩ እንዳሉም ለዋልታ ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል ከተዘዋዋሪ ፈንድ ተጠቃሚ በመሆን 11 ሆነው በመደራጀት በዘመናዊ የዶሮ እርባታ ስራ የተሰማሩ ወጣቶች ለአመታት ከቆዩባቸው ስራ አጥነት ተላቀው ተጠቃሚ እየሆኑ እንዳሉም ተናግረዋል፡፡

መንግስት ከህክምና ጀምረው የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

የጅግጅጋ ከተማ ስራ ዕድል እና የምግብ ዋስትና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱላሂ አብዲል ከተዘዋዋሪ ፈንድ በተገኘ 60 ሚሊዮን ብር በ54 ማህበራት ከ1ሺህ በላይ ስራ አጥ ወጣቶችን በማደራጀት በተለያዩ የስራ መስኮች አሰልጥነው ማሰማራታቸውን አስታውቋል፡፡

በስራቸው ውጤታማ እንዲሆኑ የከተማ አመራሩ እና ባለሙያ የቅርብ ክትትል እና ድጋፍ እያደረጉ እንደሆኑም አስረድተዋል፡፡

ፕሮግራሙ በከተማዋ የሚስተዋለውን የስራ አጥነት ሁኔታ ከመቀነስ አኳያ ፋይዳው የጎላ በመሆኑ ከተማ አስተዳደሩ በትኩረት እየሰራ እንደሆነም አተ እብዱላሂ ተናግረዋል፡፡