የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት በዛሬ ዕለት ባካሄደው የ3ኛው ዓመት የሥራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ በጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በእጩነት የቀረቡትን የ16 የካቢኔ አባላትን ሹመት በሙሉ ድምጽ አፀደቀ ።
ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ የካቢኔ ሹመቱን ሲያቀርቡ እንደገለጹት ህዝቡ የሚያነሳውን ሰላም፣ ልማትና የዴሞክራሲ ጥያቄ በብቃት ለመመለስ ለውጥ ማምጣት አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል ።
በአዲሱ የካቢኔ ሹመት የቀረቡት እጩዎች ብቃትን ፣ ልምድና የትምህርት ዝግጅትን እንዲሁም ያለፈውን የሥራ አፈጻጻም መሠረት በማድረግ የተመረጡ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል ።
በአዲስ በተደራጀው ካቤኔም የሴቶች ተሳትፎም 50 በመቶ እንዲሆን በመደረጉ በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካም የመጀመሪያ መሆኑን ጠቅላይ ሚንስትሩ አስረድተዋል ።
አዲስ የካቢኔ አባላት ሌብነትን የሚጠየፉ፣ ሃብት የማያባክንና ቅንንነት የተሞላበትን አገልግሎት የሚሠጡ መሆን ይጠበቅባቸዋል ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሩ ።
በቀጣይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሾሙ አዲስ የካቢኔ አባላት አፈጻጸምን በመከታተልና በመቆጣጣር በኩሉ የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ጠቅላይ ሚንስትሩ ጥሪ አቅርበዋል ።
የአራት የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ሚንስትሮች ባሉበት እንዲቀጥሉም መደረጉ ጠቅላይ ሚንስትሩ ገልጸዋል ።
አዲሱ የካቤኒ አባላት ሹመት ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል
- ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል የሰላም ሚኒስትር
- ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረግዛብሔር – የንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስትር
- ኢንጂነር አይሻ መሐመድ- የአገር መከላከያ ሚኒስትር
- አቶ አህመድ ሽዴ- የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትር
- አቶ ኡመር ሁሴን – የግብርና ሚኒስትር
- ወይዘሮ አዳነች አቤቤ -የገቢዎች ሚኒስትር
- ዶ/ር ኦርጌጌ ተስፋዬ – የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
- ዶ/ር ፍጹም አሰፋ – የፕላንና የልማት ሚኒስትር
- ዶ/ር ሂሩት ወልደማሪያም – የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር
- ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ- የትምህርት ሚኒስትር
- ወይዘሪት የዓለም ፀሃይ ፀጋዬ- የሴቶች ፣ ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስትር
- ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ -የትራንስፖርት ሚኒስትር
- ዶ/ር ጌታሁን መኩሪያ – የኢኖቭዬሽንና ቴክኖሎጂ ሚነስትር
- ዣንጥራር አባይ -የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር
- ዶ/ር ሳሙኤል ሆርኮ- የማዕድንና የነዳጅ ሚኒስትር
- ዶ/ር ሂሩት ካሳው – የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ናቸው ።