ምክር ቤቱ የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣውን አዋጅ አጸደቀ

የህዝብ ተወካዮች  ምክር ቤት  በዛሬው ዕለት ባካሄደው  የ3ኛ የሥራ  ዘመን  ሁለተኛ  መደበኛ ጉባኤው የ19 ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣውን አዋጅ አፅድቋል ።

ምክር ቤቱ  በመጀመሪያ  የአስፈጻሚ አካላትን  ሥልጣንና ተግባር  ለመወሰን  የወጣውን አዋጅ  እንደገና  ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅና አዲሱ የመንግሥት ተቋማዊ አደረጃጃት ላይ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ ማብራሪያ ሠጥተው ውይይት ከተደረገበት በኋላ ነው ያፀደቀው ።

ጠቅላይ ሚንስትሩ እንደገሉት  አዲሱን  የካቢኔ አደረጃጀት ለውጥ  ለማድረግ ዝርዝር  ጥናት መደረጉንና ሁሉም  ተባብሩና ተቀናጅቶ ከሥራ ውጤታማ ለመሆን የሚያስችል ነው ብለዋል ።

በረቂቅ አዋጁ መሰረትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ  ለምን አዳዲስ  የሚኒስትር መስሪያ ቤቶች  እንደገና  ማደራጀት  እንዳስፈለገ  ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረበላቸው  ጥያቄና አስተያየትም  ማብራሪያ ሠጥተውበታል ።

የህዝብ ተወካዮች  ምክር ቤትም   የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር  ለማሻሻል የወጣውን 1097 /2011 አዋጅን  በሙሉ ድምጽ  አጽድቆታል።

   

በረቂቅ  አዋጁ  መሠረትም እንደገና  እንዲደራጁ የተደረጉት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች

 

  1. የሰላም ሚኒስቴር
    2. የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር
    3. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
    4. የገንዘብ ሚኒስቴር
    5. ጠቅላይ አቃቤ ህግ
    6. የግብርና ሚኒስቴር
    7. የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር
    8. የገቢዎች ሚኒስቴር
    9. የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
    10. የትራንስፖርት ሚኒስቴር
    11. የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር
    12. የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር
    13. የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር
    14. የትምህርት ሚኒስቴር
    15. የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
    16. የጤና ሚኒስቴር
    17. የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር
    18. ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር
    19. የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር

በረቂቅ አዋጁ መሰረት በሌላ  እንዲተኩ  የተደረጉ  ሚኒስቴር መሥሪያቤቶች

  1. የፌደራል ጉዳዮችና አርብቶ አደር ሚኒስቴር – በሰላም ሚኒስቴር ተተክቷል
  2. የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት – በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት የሚተካ
  3. የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር – የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ተጠቃሏል
  4. የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር – ንግድና ኢንዱስትሪ አንድ ላይ ሆኗል
  5. የከተማ እና ቤቶች ልማት ሚኒስቴር – ከኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ጋር የተዋሃዱ