ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለፌደራል የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ሹመት ሠጡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው ዕለት ለአራት የፌደራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጡ።
 

በዚሁ መሰረት፤

1. አቶ ብናልፍ አንዱዓለም – በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ

2. አቶ መለስ ዓለሙ – በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ምክትል ዋና አስተባባሪ

3. አቶ ተመስገን ጥሩነህ – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር

4. አቶ ደሴ ዳልኬ – በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የግብርና እና የመስኖ አማካሪ በመሆን ከጥቅምት 7 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ተሾመዋል።

የተሰጠው ሹመት የትምህርት ዝግጅትና የፖለቲካ አመራር ብቃትን ከግምት ያስገባ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።