ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከሶማሊያ ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት መሀመድ አህመድና ከጠቅላይ ሚኒስትር ሀሰን ኬይሪ ጋር በአፍሪካ ቀንድ የሰላም ሁኔታ ላይ በሞቃዲሾ ውይይት አደረጉ።

ዶክተር ወርቅነህ ከሶማሊያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ለመነጋገር ከኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኡስማን ሳልህ ጋር በመሆን ትናንት ሞቃዲሾ መግባታቸው ይታወቃል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ የተፈጠረው የሰላም እና የትብብር እንዲሁም የኢኮኖሚ ውህደት ዕውን እንዲሆን እንደምትሰራ ዶክተር ወርቅነህ ለፕሬዚዳንቱ መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አመልክቷል።

ዶክተር ወርቅነህ፣ የሶማሊያና ኤርትራ አቻዎቻቸው ከዚህ ቀደም በአስመራ መገናኘታቸው የሚታወስ ሲሆን ወደ ጂቡቲ በመሄድም በአከባቢያዊ የሰላምና መረጋገት ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ይታወሳል።