ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለአፍሪካ የአመራር መጽሔት የ2018 ምርጥ አፍሪካዊ ሽልማት እጩ ሆኑ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለአፍሪካ የአመራር መጽሔት የ2018 ምርጥ አፍሪካዊ ሽልማት እጩ ሆነው ተመረጡ፡፡

በየዓመቱ በሚካሄደው በዚህ የሽልማት ዘርፍ የነዳጅ ላኪ አገራት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ናይጄሪያዊው መሐመድ ሳኑሲ ባርኪንዶ እና የቀድሞው የቦትስዋና ፕሬዝዳንት ሴሬትሳ ካማ ኢያን ካማ ከዶክተር አብይ ጋር በእጩነት ቀርበዋል፡፡

የሽልማቱ አሸናፊ የሚለየው በመጽሔቱ ድረ-ገፅ ላይ በኢንተርኔት በሚሰጥ ድምፅ ሲሆን እስካሁን ዶክተር አብይ ከዘጠና በመቶ በላይ ድምጽ በማግኘት ተፎካካሪዎቻቸውን እየመሩ ነው፡፡

ድምጽ የሚሰጥበት ጊዜም እስከ ታህሳስ 1፤2011 ዓ.ም ድረስ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ይህ ታዋቂ ሽልማት በተለያዮ ዘርፎች የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የአፍሪካ የቢዝነስ፣ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ መሪዎች እውቅና የሚሰጥ ነው ሲል አፍሪካ ሊደርሺፕ ዶት ኮም ዘግቧል፡፡