ሴቶች በሰላምና በግጭት አፈታት ላይ ያላቸውን ሚና ለማጎልበት የተጠናከረ ሥራ መሥራት እንደሚገባቸው በዛሬው ዕለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተካሄደው ውይይት ተገለጸ ።
የሰላም ሚኒስቴርና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጋራ ሆነው ባዘጋጁት የሴት አፈጉባኤዎች መድረክ ላይ እንደተገለጸው ሴቶች በአገሪቱ ሰላምና ግጭት አፈታት ላይ ያላቸውን ሚና ይበልጥ ለማጎልበት እንደሚሠሩ ገልጸዋል ።
በውይይት መድረኩ ላይ በዘጠኝ ክልሎች፣በሁለት ከተሞች ከወረዳ እስከ ክልልና ከተማ ምክር ቤቶች ውስጥ እያገለገሉ የሚገኙ አፈጉባኤዎች ተገኝተዋል ።
ሴቶች ግጭትን በመፍታት ረገድና የሰላም እሴትን በመገንባት ረገድ ያላቸውን መሪ ሚና እንዴት ማሳደግ እንዳለባቸው የሚያሳይ ጥናታዊ ጽሑፍ በወይዘሮ ሙባ መሐመድ ቀርቧል ።
ሴት አፈጉባኤዎችን ያሳተፈው ይህ ጉባኤ “ ሴት አፈጉባኤዎች ለሰላም” በሚል መሪ ቃል ነው የተካሄደው ።
በመድረኩ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ኬሪያድ ኢብራሂም ተገኝተዋል ።