ህንድ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በህጋዊ ፍቃድ እንዲንቀሳቀሱ አዲስ አሰራር አወጣች

ህንድ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በህጋዊ ፍቃድ እንዲንቀሳቀሱ አዲስ አሠራር ማውጣቷ ተገለጸ፡፡

ህንድ ይህንን ያደረገችው በሲቪል አቬሽን ሚኒስቴር በኩል ሲሆን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን የሚያንቀሳቅሱ ድርጅቶችና ግለሰቦች የመለያ ቁጥር ተሠጥቷቸው ክፍያ እንዲፈጽሙ ይደረጋል ነው የተባለው፡፡  

ሀገሪቱ በሰው አልባ አውሮፕላን ቴክኖሎጂ ከቀዳሚዎቹ ተርታ የምትሰለፍ ሲሆን ወደ ውጪ ሀገራትም በመላክ ትታወቃለች፡፡

አሁን በሚጀመረው ምዝገባ መሠረት እያንዳንዳቸው ሰው አልባ አውሮፕላኖች በተዘጋጀው አዲስ መተግበሪያ የሚንቀሳቀሱበትን ሥፍራና ጊዜ እንዲያሳውቁ ያደርጋል ተብሏል፡፡

በመሆኑም ሰው አልባ አውሮፕላኖቹ አረንጓዴ ተብሎ በተለየው የአየር ክልል ውስጥ ለመብረር መተግበሪያው ጊዜና ትክክለኛ ቦታ ማሳወቅ የሚጠበቅባቸው ሲሆን በቢጫ ክልል ውስጥ ግን ፍቃድ እንደሚያስፈልጋቸው ተደንግጓል፡፡ 

በሌላ በኩል በቀይ የበረራ ዞን ወስጥ ግን ሰው አልባ አውሮፕላኖች መግባት ፈጽሞ የተከለከለ ነው ተብሏል፡፡ (ሲጂቲኤን)