በአማራና ቅማንት ማህበረሰቦች መካከል ለተፈጠረውቁርሾ እልባት ለመሥጠት የሚያስችል የሰላምና የእርቅ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

በአማራ እና ቅማንት ማህበረሰቦች መካከል ለተፈጠረው ቁርሾ እልባት ለመሥጠት ያለመ ህዝባዊ የሰላምና የእርቅ ጉባኤ በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

የጉባኤው ዓላማ በክልሉ በተለይ በማዕከላዊና ሰሜን ጎንደር ዞኖች የተከሰቱ ማንነትን መሠረት ያደረጉ ግጭቶችን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለመፍታት መሆኑ ተገልጿል፡፡

በጉባኤው ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

ተሳታፊዎቹ በተጠቀሱት አካባቢዎች በየጊዜው የሚከሰቱ ግጭቶችንና መፈናቀሎችን ለማስቆም የኃይማኖት አባቶችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በሚኖራቸው ሚና ላይ ምክክር ያደርጋሉ ተብሏል፡፡

በአማራ ክልል በተለያዩ ጊዜያት ከተከሰቱት ግጭቶች ጋር ተያይዞ 30 ሺህ የሚደርሱ ተፈናቀዮች መኖራቸውን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ላቀ አያሌው ገልፀዋል፡፡ (ምንጭ፡- ኢቲቪ)