የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ በዛሬው ዕለት መካሄድ ጀምሯል።
ምክር ቤቱ ለሶስት ቀናት በሚያካሂደው መደበኛ ጉባኤ የአስተዳድሩን የ2012 ረቂቅ በጀት ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ከዚህ ባለፈም የተለያዩ ሹመቶችን የሚያፀድቅ መሆኑ ተገልጿል።
እንዲሁም ምክር ቤቱ የከተማዋን ፍርድ ቤቶች የ2011 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን በማዳመጥ የሚያፀድቅ መሆኑን ከወጣው መርሃ ግብር ለማወቅ ተችሏል።።
ጉባኤው ለሶስት ቀናት እንደሚቀጥል ከአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡