የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀምሯል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ ጉባኤ የአስፈጻሚው አካል የ2011 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን አድምጧል።

በሪፖርቱ ላይ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በማንሳትም ውይይት ተካሂዶበታል።

ምክር ቤቱ ለ2012 በጀት ዓመት ለአስተዳደሩ በቀረበው 2 ቢሊየን 834 ሚሊየን 440 ሺህ ብር ረቂቅ በጀት ላይ ተወያይቶ ያጸድቃል ተብሎም ይጠበቃል።

ምክር ቤቱ በመጨረሻም የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ የሁለት ቀናት ጉባኤውን የሚያጠናቅቅ ይጠበቃል።