ሃረማያ ዩንቨርስቲ ከዓለም ባንክ የ6 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አገኘ

አዲስ አበባ ሐምሌ 18/2008 (ዋኢማ)-የሃረማያ ዩንቨርስቲ የአፍሪካ የምርምር እና የልእቀት ማእከል ለመሆን የሚያደርገውን ጥረት የሚደግፍ የ6 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ከአለም ባንክ አገኘ።

ድጋፉ ዩንቨርስቲው ከአየር ንብረት ጋር ተመጋጋቢ የሆነ እና የግብርናውን ዘርፍ የሚደግፉ የትምህርት መስኮች ላይ የልህቀት ማዕከል ለመሆን የሚያደርገውን ጥረት እንደሚያግዝ ተነግሯል።

አለም ባንክ ባለፈው ዓምት ከግብርናው ዘርፍ ጋር በተያያዘ የብዛ ህይወትን የሚያስቀጥል የተሻለ እቅድ ላቀረቡ ዩንቨርስቲዎች ድጋፍ እንደሚያደርግ መግለጹ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎ የአየር ንብረት ለውጥን ሊቋቋም የሚችል ግብርና እና ብዛሃ ህይወትን መጠበቅ ይቻላል በሚለው ጥናታዊ ፅሁፉ የሃረማያ ዩኒቨርሲቲ ድጋፉን እንዲያገኝ አስችሎታል።

የሃረማያ ዩንቨርስቲ የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዘዳንት ፕሮፌሰር ንጉሴ ደቻሳ፥ የግብርናው ዘርፍ የልህቀት ማዕከላችን ለማጠናከር ድጋፉ ወሳኝነት አለው ብለዋል።

ድጋፉ በሁለተኛ ድግሪ እና በሶስተኛ ዲግሪ ዩንቨርስቲው በሚሰጣቸዉ የትምህርት መስኮች ማስተግበሪያም እንደሚሆን ጨምረዉ ገልፀዋል።(ኤፍ.ቢ.ሲ)