በሳውዲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው የሚመለሱበት ለአንድ ወር መራዘሙን ሚኒስቴሩ አስታወቀ

በሳውዲ አረቢያ ለሚገኙ ተመላሽ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው የሚመለሱበት ጊዜ ለ30 ቀናት ያህል መራዘሙን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽሕፈቤት ዛሬ ለዋልታ በላከው መግለጫ ፤ይህ የእፎይታ ጊዜ የኢፌዲሪ መንግስት የዲፕሎማሲ ጥረት ውጤት ነው ብሏል ፡፡

በሳውዲ የሚገኙ የተሰጠውን የእፎይታ ጊዜ ተጠቅመው  ዜጎቻችን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥሪውን አቅርቧል  ፡፡ 

 

በትናትናው እለት 1ሺ 130 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ገብተዋል ያለው መግለጫው፤መንግስት ዜጎች ወደአገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ጥረቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ያስታወቀው ፡፡

መግለጫው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ የእፎይታ ጊዜ እንዲሰጥ የሳውዲ አረቢያን መንግስት መጠየቃቸው አስታውሷል ፡፡