ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሕዝቦች ለጋራ ልማት በአንድነት እንዲነሱ ያደረጉት አስተዋጽኦ ታሪክ ሲዘክረው እንደሚኖር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታወቀ ።
ምክር ቤቱ ለዋልታ በላከው መግለጫ እንደገለጸው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሆኑን ሲያገለግሉ የቆዩት ኢንጂነር ስመኘው በህይወት ብናጣቸውም ብሔሮች ፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በአንድነት ለጋራ ልማት እንዲነሱ ያደረጉት አስተዋጽኦ ትውልድና ታሪክ ይዘክረዋል ብሏል ።
በኢንጂነር ስመኘው በቀለ ድንገተኛ ህልፈት ምክንያት የምክር ቤቱ ሠራተኞች ድንጋጤ ቢሰማቸውም መላው የአገሪቱ ህዝቦችን በበለጠ ህዝባዊ አንድነትና የጋለ ወኔ በማስተባበር ግድቡን በማጠናቀቅ የቆምንለትን ዓላማ እናሳካለን ብሏል በመግለጫው ።