የጤና ዘርፍ ባለሙያዎችና አመራሮች በትግራይ ክልል የሚገኙ የጤና አገልግሎት መስጪያ ተቋማትን ጎበኙ

በመቐለ ከተማ በሚካሄደው 20ኛው የጤና ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ የሚሳተፉ የጤና ዘርፍ ባለሙያዎች፣ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት በትግራይ ክልል የሚገኙ የተለያዩ የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ጎበኙ ።  

የጤና ዘርፉ ባለሞያዎች፣ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት በትግራይ ክልል ህብረተሰቡን የተሻለ  ተጠቃሚ ለማድረግ የተሠሩትን  የተለያዩ የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ጎብኝተዋል፡፡

በመስክ ምልከታ ወቅትም በክልሉ በጤና ዘርፍ የሚገኘውን ተሞክሮ በመውሰድ በቀጣይ ለሚዘጋጁ እቅዶችና ለችግሮች አፈታት በግብአትነት ለመጠቀም የሚረዳ መሆኑን በጉብኝቱ ወቅት ተነሰቷል፡፡

በትግራይ ክልል በጤና አገልግሎት መስጪያ ተቋማት ላይ በተደረገው የመስክ ጉብኝትም  የፊደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትሮች የክልል የጤና ቢሮ ኃላፊዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላትም ተሳትፈዋል፡፡

ለ20ኛ ጊዜ በሚካሄደው ሀገር አቀፍ የጤና ዘርፍ ጉባኤ ክልሎች ባለፈው በጀት አመት ያከናወኗቸው ተግባራትን ሪፖርት በማቅረብ ውይይት የሚያካሂዱበት መድረክ ይሆናልም ተብሎ ይጠበቃል፡፡

“ሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋን ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ጠንካራ የጤና ስርአት መገንባት ” በሚል መሪ ቃል የሚከናወነው 20ኛው ሀገር አቀፍ የጤና ዘርፍ ጉባኤ በመቐለ ከተማ ከህዳር 14 እስከ 16 ድረስ ለሦስት ቀናት ይከናወናል ፡፡

20ኛው የጤና ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ  በዛሬው ዕለት  በመቐለ ከተማ የተጀመረ  ሲሆን  ከፌደራል የጤና ጥበቃ  ሚኒስቴር ፣ የክልሎች የጤና ቢሮ ኃላፊዎች ፣ ባለድርሻ አካላትና የጤና ባለሙያዎች እየተሳተፉ  ይገኛል  ።