ከሶስት አመት በፊት ሊቢያ ላይ በአይሲስ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ 34 ኢትዮጵያውያን አፅም መገኘቱ ተገለጸ

ከሶስት ዓመት በፊት በፅንፈኛው አሸባሪ ቡድን አይ ኤሲ አይ ኤስ ሊቢያ ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ 34 ኢትዮጵያውያን አፅምን ማግኘታቸውን የሊቢያ ባለስልጣናት አስታወቁ።

የሊቢያ የወንጀል ምርመራ መምሪያ ባለስልጣናትን ዋቢ አድርጎ ሬውተርስ እንደዘገበው ተይዞ ምርመራ ሲደረገበት የነበረ የአሸባሪ ቡድኑ አባል የሰጠውን መረጃ መሰረት በማድረግ በተከናወነ ምርመራ ነው ኢትዮጵያውያኑ የተቀበሩበት የጅምላ መቃበር የተገኘው።

መምሪያው ያወጣው በድሮን የተቀረፀ ቪዲዮም ሲርጥ ተብላ በምትታወቀው የሊቢያ የባህር ዳርቻ አቅራቢያ በሚገኝ እርሻ ውስጥ የጅምላ መቃብሩ መገኘቱ ነው የተገለጸው፡፡

የኢትዮጵያውያኑ አፅም ተገቢው የህግ ስራ ከተከናወነ በኋላም ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያ እንደሚላክም ባለስልጣናቱ አስታውቀዋል።