ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ ከዋተር ኤድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጋር ተወያዩ

ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የዋተር ኤድ ዋና ስራ አስፈጻሚን ቲም ዊን ራይትን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡ 

የዋተር ኤድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዊን ራይት ወተር ኤድ የውሃ አቅርቦትን ለማዳረስ የሚያከናውናቸውን ተግባራት በተመለከተ ለፕሬዝደንቷ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡

ከፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በተለይም በኢትዮጵያ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን ለማዳረስ እና ንጹህ አካባቢን ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ዋተር ኤድ የሚያደርጋቸውን እንቅስቃሴዎች አብራርተዋል፡፡

ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በበኩላቸው ድርጅቱ የሚያከናውናቸው ስራዎች መልካም መሆናቸውን ጠቅሰው በቀጣይነትም አጠናከሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡