ቻይና 206 ሚሊየን ብር የሚያወጣ እህል ለገሰች

የቻይና መንግስት 206 ሚሊየን ብር የሚያወጣ 7ሺህ 408 ሜትሪክ ቶን ስንዴና 579 ሜትሪክ ቶን ነጭ ሩዝ የሰብዓዊ እርዳታ ማድረጉ ተገለጸ፡፡

ድጋፉ የተከናወነው ቀደም ሲል የሁለቱ አገሮች መንግስታት ባደረጉት ስምምነት መሰረት ነው፡፡

የብሄራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሣ ድጋፉ በሀገሪቱ በተከሰቱ ግጭቶች ለተፈናቀሉ እና ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ለሚኖሩ ዜጎች እንዲውል እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡ የቻይና መንግሰትም ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ታን ጂያን በበኩላቸው እንደኢትዮጵያ በማደግ ላይ ያሉ አገራት የምግብ ዋስትናቸውን በዘላቂነት ለማረጋገጥ ግብርናቸውን ማዘመን እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡

በመድረኩ የተሳተፉት ሌሎች አገራትም ከዚህ ቀደም መቶ ሚሊየን የቻይና ገንዘብ ዮዋን በየዓመቱ በቀጣይነት ለመስጠት ቃል ገብተው የነበረ ሲሆን፣ ይህን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈርሟል፡፡