የኢንቨስትመንትና የስራ ፈጠራ ብሔራዊ ኮሚቴ አባላት ይፋ ሆኑ

የኢንቨስትመንትና የስራ ፈጠራ ብሔራዊ ኮሚቴን አባላት ይፋ ሆኑ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢንቨስትመንትና የስራ ፈጠራ ብሔራዊ ኮሚቴን ዛሬ ይፋ አድርገዋል፡፡

ኮሚቴው በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ ሲሆን፣ በውስጡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ፣ የዘጠኙ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች፣ የአዲስ አበባና የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች፣ ሁለት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ተወካዮችና 10 የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን ያቀፈ ነው፡፡ የዘገበው ኢቢሲ ነው፡፡